ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በመደጋገፍና በአንድነት ማለፍ ይገባል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በመደጋገፍና በአንድነት ማለፍ ይገባናል” ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
የጤና ሚኒስቴር በአፋር ክልል ፈንቲ ረሱ ዞን በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው ጤና ተቋማት ስራ ማስጀመሪያ የሚውል 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የህክምና መርጃ መሳሪያ ዛሬ ድጋፍ ተደርጓል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አስረክበዋል።
“በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በመደጋገፍና በአንድነት ማለፍ ይገባል” ያሉት ሚኒስትሯ፤ ለክልሉ የተሰጠው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል።
ጤና ሚኒስቴር የህክምና መረጃ ቁሳቁስ ድጋፋ ያደረገው በክልሉ በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት ለደረሰባቸው አምስት የጤና ተቋማት ስራ ለማስጀመር መሆኑ ነው የተገለጸው።
የሚኒስቴሩ ድጋፍ የህክምና ተቋማቱ ወደ ስራ እንዲገቡና ድንገተኛና መደበኛ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ እገዛ እንደሚያደርግ ዶክተር ሊያ ጠቁመዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው ፤ አሸባሪው ህወሓት በአፋርና አማራ ክልሎች ላይ ንጹሐንን ገድሏል፤ የዜጎች ሀብት ንብረት ላይ ዘረፋ ፈጽሟል።
ይህ አሸባሪ ቡድን ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እናቶችና ህጻናትን እየገደለ መሆኑን ገልጸዋል።
የዚህ አሸባሪ ጨካኝና አረመኔ ቡድን ድርጊት ለታሪክ የሚቀመጥ መሆኑን ገልጸው፤ የጤና ሚኒስቴር በወሳኝ ወቅት ድጋፍ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
ይህ የአሸባሪ ቡድን ድርጊት “በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ይመከታል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!