Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ የተካሄደው የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ የስራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁ የጉባኤው አባላት ሽኝት በማድረግ አዲስ አባላትን ሾሟል።

አዲስ የጉባኤው አባላትም ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።

አዲስ የጉባኤው አባላትም አቶ ሙህየዲን አህመድን በድጋሚ የጉባኤው አፈጉባኤ አድርገው ሲሾሙ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ ደግሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተሹመዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የጉባኤ አባላት ባለፉት አመታት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አባላቱ ባለፉት አመታት ያጋጠሙ ችግሮች እንዲፈቱ ከማድረግ አንፃር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አንስተዋል።

“በቀጣይም የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅትና በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

ከሌሎች ወንድም እህቶች ጋር ያለውን አንድነትና ቁርኝት በማጠናከር ህዝብን ማዕከል ያደረጉ ስራዎች መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የምክር ቤቱ ዋናና ምክትል አፈጉባኤ ሆነው የተሾሙት አቶ ሙህየዲን አህመድና ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ ህዝቡን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ቃል ገብተዋል።

አቶ ሙህየዲን ላለፉት አመታት የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈጉባኤ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.