Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ የሚኒስትሮች ጉባዔ በጂቡቲ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በላባደሮች፣ ስራ፣ ስራ ፍለጋ የሚሰደዱ ሰዎች ዙሪያ ዋነኛ የመወያያ አጀንዳቸው አድርገዋል፡፡

በጉባዔው የኢጋድ ሚኒስትሮች ፣ አምባሳደሮች፣ አባለ ሀገራት እና የተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል ፡፡

ውይይቱ ቀጠናዊ ትስስር በማጠናከር በሰራተኞች አስተዳደር፣ በስራ እና ለስራ ፍለጋ የሚሰደዱ ሰዎች የተመለከተ ወጥ ሰርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል እና ወደ ተጨባጭ ስራ የሚያሰገባ መደላደልን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የጂቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል መሃመድ ÷ የኢጋድ የወቅቱ ዋና ፀሐፊ  ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የዓለም አቀፉ የሠራተኛ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አሌክሲዮ ሙሲንዶ በተገኙበት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያን ወክለው በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ በጉባዔው ተሳትፈዋል፡፡

አምባሳደር ብርሃኑ ከየአባል ሃገሩ የሚመጡ የውጭ ሃገር ስደተኛ ሠራተኞችን የሥራ ሁኔታ ለማሳደግ በቀጠናው ተስማሚ ፖሊሲና መመሪያ መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት መስጠታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.