የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ስራን ለማሳካት የክተት አዋጅ በማድረግ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል – የክልሉ ትምህርት ቢሮ

By Feven Bishaw

October 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር አጠቃላይ የትምህርት አጀማመር እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት አተገባበር ሒደት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡

የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ ÷ትምህርት ስራ ሁሉንም የሚመለከት በመሆኑ ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።