Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ማህበር አባል ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ማህበር አባል ለመሆን የቻለው ያቀረበው ማመልከቻና መረጃ ተቀባይነት በማግኘቱ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
 
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በማህበሩ አባል መሆን ከዩኒቨርሲቲው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ አንዱ አቢይ ጉዳይ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር አባል መሆኑ የግንኙነት መረብ በመዘርጋት ከዉጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነቶችን ለማድረግ ምቹ ሁኔታዎች ይፈጥርለታል ነው የተባለው፡፡
 
በተጨማሪም ከማህበሩ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እንደሚያገኝና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር እንደሚረዳው ከዩኒቭርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.