Fana: At a Speed of Life!

ለወታደራዊ ባህርተኞች የውሃ ዋና ሥልጠና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በውሃ ዋና የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል የውሃ ዋና ሥልጠና ለወታደራዊ ባህርተኞች ተሰጠ

ቢሾፍቱ የሚገኙትን የባህር ሃይል መሠረታዊ ባህርተኞች የመጀመሪያ ደረጃ በውሃ ዋና የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የመከላከያ ባህር ሃይል ም/አዛዥ ለሎጅስቲክስ ኮሞዶር ዋለፃ ዋቻ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ÷ የሃገርን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችልና ከውስጥና ከውጭ የሚመጡ ችግሮችን የሚመክት ዘመናዊ የሆነ ባህር ሃይል መገንባት ማደራጀትና ማሰልጠን አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የወታደራዊ ዲፕሎማሲ አካል ትብብር ውስጥ በመታቀፍ የውጭ ሀገር ጉብኝትና የልምድ መቅሰም ፣ በጠቅላይ መምሪያው ለመላው ባህር ሃይል ስታፍ አባላት የውስጥ አቅም ግንባታ ፣ በተመረጡ ውጭ ሀገራትና በሀገር ውስጥ አጫጭር ስልጠናዎች ማከናወን የተቻለ መሆኑን ም/አዛዡ አመልክተዋል፡፡

ከመከላከያ ጋር ወታደራዊ ትብብር ካላችው የውጭ ሀገራት የእጩ መኮንን ስልጠናዎችና ባህርዳር ማሪታይም አካዳሚ በመላክ በኤሌክትሪካልና መካኒካል የኢንጂነሪንግ መስክ ሥልጠናዎችን ማከናወን መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

አዛዡ በውጭ ሀገር ያገኘነው የስልጠና አቅም የኢትዮጵያን ባህር ሃይል በፍጥነት ለግዳጅ ዝግጁ ከማድረግ አንፃር ጠቀሜታው ስትራተጂካዊ መሆኑን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የውሃ ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ሻለቃ ባሻ ፍሰሃ ሃይሉ ÷ በውሃ ዋና የሚሰጡ ግዳጆችን ለመወጣት የሚያስችል የውሃ ዋና ሥልጠና ለወታደራዊ ባህርተኞች ጠንካራና ብቃት ያለው ፣ በየትኛውም የውሃ አካል ላይ ግዳጅን መወጣት የሚያስችልና በመከላከያ ሃይላችን ላይ ተጨማሪ የማድረግ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ሰልጣኝ ባህርተኞች እንደተናገሩት ÷ ስልጠናው ቀጣይ የሚሰጠን ግዳጅ በዋናነት የባህር ላይ ደህንነት፣ ፀረ- ሽብር፣ የባህር ላይ ውንብድና ወዘተ የመከላከል እና ብሔራዊ ጥቅማችንን ከምንጊዜውም በላይ ለማስጠበቅ በእልህና ወኔ የመጀመሪያውን በውሃ ዋና የሚሰጥ ግዳጅ ሥልጠና አጠናቀናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.