ስፓርት

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር መር ሃ ግብር ይፋ ሆነ

By Meseret Awoke

October 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት /ሴካፋ/ የ2021 ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል እንደሚደረግ የውድድሩ አዘጋጀች አሳውቀዋል፡፡

ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 30 / 2014 ዓ.ም በዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር ላይ ስድስት ሀገራት በዙር መልኩ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ ተብሏል፡፡

አዘጋጇ ዩጋንዳ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ብሩንዲ ፣ ኤርትራ ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ በውድድሩ ላይ ተካፋይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ውድድሩ በሊግ አደረጃጀት የሚከናወን ሲሆን÷ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበ ተወዳዳሪ ሀገር አሸናፊ በመሆን ውድድሩን ያጠናቅቃል፡፡

ተወዳዳሪ ሀገራት ውድድሩ ከሚጀመርበት ሁለት ቀናት አስቀድሞ ዩጋንዳ ካምፖላ መግባት እንደሚችሉ አወዳዳሪው አካል አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በወጣው ፕሮግራም መሠረት የመጀመሪያውን ጨዋታ ጥቅምት 20/2014 ከቀኑ 7:30 ከጅቡቲ አቻው ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ውድድሩን እንደሚጀምር ከስፖርት ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያ የምታደርጋቸው ጨዋታዎች መር ሃ ግብርም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ጥቅምት 20/2014 – ኢትዮጵያ ከ ጅቡቲ (7:30)

ጥቅምት 22/2014 – ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ (7:30)

ጥቅምት 24/2014 – ታንዛንያ ከ ኢትዮጵያ (4:30)

ጥቅምት 27/2014 – ከቡሩንዲ ከ ኢትዮጵያ (4:30)

ጥቅምት 30/2014 –ዩጋንዳ ከ ኢትዮጵያ (10:00)

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!