የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አያኖ በራሶ ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ ዶክተር አያኖ በራሶ እንደገለጹት÷ ስምምነቱ ሁለቱም አካላት በተጠናከረ የአሠራር ስልት ተሳስረው ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችላቸው ነው ማለታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ በበኩላቸው÷ ከሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ከውጪ ምንዛሪ ግኝት እና ከዕውቀት ሽግግር አንጻር ሀላፊነት እንደተቀበልን እናስባለን ፤ ይህን ታሳቢ በማድረግም ችግሮችን ተቀራርቦ ለመቅረፍ ሰፊ ግንኙነት መጀመራችን ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ፋሲካ በቴ ÷ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ጋር በቅርበት እየሠሩ እንደነበረና በዚህም በ2013 በጀት ዓመት ከ200 የሚበልጡ ተመራቂዎች በኢንዱስትሪ ፓርኩ ሊቀጠሩ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!