ወ/ሮ አዳነች ለአቶ ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ለተሾሙት አቶ ኦርዲን በድሪ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ታላቅ የህዝብ አደራን ለተቀበሉት አቶ ኦርዲን በድሪ በራሴና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስም እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡
ስኬታማ የአገልጋይነት ዘመን ይሁንልዎት ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!