Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አማካኝነት ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የታደሱ ቤቶችን አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በትራንስፖርት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት አማካኝነት በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጉለሌ ከተማ ክፍለ ከተማ የታደሱ ቤቶችን በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡

ባለፉት ወራት በክረምት የበጎ ቃድ አገልግሎት መርሀ ግብር ከ2ሺህ በላይ ቤቶችን እድሳት በማድረግ፣ ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ያጡ ህጻናት በማሳደግ ፣ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ በማሰባሰብ እና በልዩ ልዩ ተግባራት መሰራታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡

መረዳዳት እና መተጋገዝ የኢትዮጵያዊያን ባህል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷ በክረምት በጎ ፍቃድ መርሃግብርም የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በተለያ የበጎ አድራጎት ሥራ የተሳተፉ ተቋማት እና ግለሰቦች እንዲሁም ወጣቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ወ/ሮ እቴነሽ ዘርፉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት የሚኖሩ አቅመ ደካማ እናት ሲሆኑ ÷ ቤታቸው ፈርሶ በተለይ በክረምት ወራት መኖር እስኪከብዳቸው ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡

ዛሬ ግን እንደ አዲስ ተወለድኩኝ ያሉት እናት የተደረገላቸውን የቤት እድሳት አመስግነዋል፡፡

ለወይዘሮ እቴነሽም በየወሩ የ1 ሺህ አስቤዛ ለመስጠት ከንቲባዋ ቃል የገቡ ሲሆን ÷ ሌሎች በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችም በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቅድስት ተስፋዬ

ተጨማሪ መረጃ – የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.