Fana: At a Speed of Life!

በቦረና የተከሰተው ድርቅ ቀድሞ መዘጋጀት ባይቻል ኖሮ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ያደርስ ነበር – የክልሉ መንግሰት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በቦረና የተከሰተው ድርቅ ቀድሞ መዘጋጀት ባይቻል ኖሮ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ያደርስ ነበር ሲል የኦሮሚያ ክልል መንግሰት ገልጿል።

የክልሉ የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ሀይሉ እንደገለፁት ÷በቦረና የተከሰተው ድርቅ መንግሰት ቀድሞ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የሰራው ስራ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ አድርጓል ብለዋል ።

በእንስሳት ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ከመደበኛ በጀት ውጪ 100 ሚሊየን ብር በመመደብ እየሰራ እንደሆነ አመላክተዋል።

ከዚህ ውስጥም 10 ሚሊየን ለመኖ ፤ 20 ሚሊየን ደግሞ ለውሃ ተመድቦ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም የመኖ አቅርቦት እንዲኖር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና በኪራይ የተያዙ ፣ ግለሰቦች ያበረከቷቸው እንዲሁም የኮንሶ ወረዳ የሰጣቸው ቦቴዎችን ጨምሮ 16 የውሃ ቦቴዎችን በመጠቀም ውሃ የማመላለስ ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት።

በጊዜያዊነት ከሚሰሩት ስራዎች ባሻገር 1 ቢሊየን ብር ተመድቦ ግዙፍ የውሃ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ለቦረና የሚደረገው ድጋፍ በበርካታ ወገኖች እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ÷ ይህም በችግር ጊዜ አብረን ለመቆም ያለንን ቁርጠኝነት ያሳየ ነው ብለዋል።

ድጋፍ ማደረግ የሚሹ አካላትም ድጋፉን በማዕከልነት ለማሳሰባሰብ በተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ብቻ እንዲሆንም አሳስበዋል።

ከፀጥታ ጋር በተገናኘ የህዋሓትን አጀንዳ ለማስፈፀም የሚውተረተረው ኦነግ ሸኔን ለመመከት ጠንካራ ስራ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት ሃላፊው ÷ በሁሉም ወረዳና ቀበሌዎች ጥቃቱን መመከት የሚያስችል አደረጃጀት መፈጠሩን ገልፀዋል።

ቡድኑ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ የብሄር መልክ ለመስጠት ያቀደው ግጭትም በህዝቡ አርቆ አሳቢነት ከሽፏል ነው ያሉት።

ቡድኑ ከአዲሱ መንግስት ምስረታ በኋላም በቀደመ ባህሪው ቀጥሎ ‘ሰላም የለም’ የሚለውን ለማስተጋባት በየአካባቢው ግድያዎችን እየፈፀመ ነው ያሉት አቶ ሀይሉ÷ በተጨባጭ ህብረተሰቡ የቡድኑን አጥፊነትና ጠላትነት ያረጋገጠ በመሆኑ ሃሳቡ እንደማይሰምረለት ያረጋገጠበት መሆኑን አንስተዋል።

ህዝቡ የሁልጊዜ ትብበሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.