Fana: At a Speed of Life!

የሲሚንቶ ምርትን ለመጨመር የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶ ምርትን መጨመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ከሲሚንቶ ፋብሪካ አመራሮች ጋር ምክክር መካሄዱን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ኢንጂነር ታከለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉትም ÷ በውይይቱ ከአመራሮቹ ጋር የሲሚንቶ ምርት መጨመር በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ተወያይተን መግባባት ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

ከተወሰኑ ወራት በኃላ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የድንጋይ ከሰል ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ለመተካት መግባባት ላይ መድረሳቸውንም ነው የገለጹት፡፡

በሲሚንቶ አምራቾች በኩል የተነሱ የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግሮችንም እንፈታለን ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

አክለውም በየትኛውም ዘርፍ ወደፊት ለመጓዝ ስናስብ ሀገራዊ እድገታችንን የሚመጥን አቅርቦት ያስፈልገናል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.