Fana: At a Speed of Life!

በፌስቡክ የተዋወቁ ወጣቶች ከ246 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ቴምር ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በፌስቡክ የተዋወቁ 10 ወጣቶች “ቴምር ለጀግኖቻችን ስንቅ” በሚል መሪ ቃል ከ246 ሺህ ብር በላይ አሰባስበው የገዙትን ቴምር ለመከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀኔራል አስረስ አያሌው÷ወጣቶቹ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለመልካም ተግባር በመጠቀም ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ማንኛውም የማህበራዊ አንቂ ሀገርን ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለመልካም ተግባር እንዲጠቀምበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአሸባሪው ህውሃት በአማራ እና አፋር ክልሎች ከሚፈጽማቸው በርካታ ግፎች በተጨማሪ የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም በሚነዛው አሉባልታ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦና ጫና በማህበረሰቡ ላይ እየፈጠረ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሀገር ውስጥና ለውጭው ማህበረሰብ እውነተኛ መረጃ በማድረስ አሸባሪው ህወሓት የሚያስተላልፈውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ማክሸፍ ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡
ድጋፉን ያደረጉት ወጣቶች በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያን ለማዳን የምንችለውን ሃላፊነት ለመወጣት እና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን መሆናችንን ለማሳየት ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡
በቅድስት አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.