Fana: At a Speed of Life!

የአንድን ብሔር ሳይሆን የሁሉንም ህዝቦች እኩል ተጠቃሚነት ለማጎልበት መስራት ይገባል-አቶ ኦርዲን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ የክልሉ የካቢኔ አባላት የአንድን ብሔር ሳይሆን የሁሉንም ህዝቦች እኩል ተጠቃሚነት ለማጎልበት መስራት እንደሚገባቸው የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡
 
የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የመጀመሪውን ውይይት በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል፡፡
 
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በአዲስ መልክ የተቋቋመው ካቢኔ የተጣለበትን የህዝብ እና የመንግስት አደራ በላቀ ተነሳሽነት መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡
 
የካቢኔ አባላቱ ሁሉንም የክልሉን ህዝቦች በፍትሀዊነት ማገልገል እንዳለባቸውም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት።
 
አመራሩ የተሰጠውን ህዝብን የማገልገል ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ÷በቀጣይ የ100 ቀናት ዕቅድ በማውጣት የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስ የሚያስችሉ ስራዎችን በአፋጣኝ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
 
የአገልጋይነት ስሜትን በማጎልበትና በተሰማሩበት የስራ መስክ አርአያ የሚሆኑ ተግባራትን ለማከናወን ርብርብ ማድረግ ይገባል ማለታቸውንም ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታለ፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.