አዋሽ ባንክ በጎርፍ አደጋ ለተጠቃው የመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ በቅርቡ በመዲዋ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰበት የመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ባሳለፍነው ነሐሴ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ላይ ጉዳት ከማድረሱ ባለፈ በቅጥር ግቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል፡፡
በቤተክርስቲያኗ ላይ መሰል አሳዛኝ አደጋ ሊከሰት የሚችልበትን ሁኔታ ለመቀነስ እና በአደጋው የተጎዱ ህንፃዎችን ለመጠገን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ አዋሽ ባንክ የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጸሃይ ሽፈራው÷ባንኩ ከህብረተሰቡ ጋር አብሮ ማደግ የሚለውን መርህ ዕውን ለማድረግ የህብረተሰቡን ኑሮ በሚለውጡ ፕሮጀክቶች ላይ ከሚሠሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በመስራት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም በማንኛውም ወቅት ድንገተኛ አደጋዎች በሚያጋጥሙ ጊዜም ከማህበረሰቡ ጎን መቆሙን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!