Fana: At a Speed of Life!

በወሎ የጁንታው መጨረሻ እየቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ቦሩ ሥላሴ አካባቢ ለጥፋት ተሰልፎ የመጣው ጠላት በመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ በሚሊሻውና በፋኖው ጥምረት ተጠራርጎ ከመሳህል ወደ ማርዬ እየተመታ እየሸሸ ነው።
የአካባቢው ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ከሠራዊቱ ጋር በመሆን ሸጦችንና ጉድባዎችን እየዘጋ ወራሪውን መግቢያና መውጫ እንዳያገኝ እያደረገው ይገኛል።
በሐይቅ አካበቢ የመጣውም ተመትቶ ወደ ሱሉሌ እና ወደ ባሶ ሚሌ አቅጣጫ እየፈረጠጠ ይገኛል። በተመሳሳይም ከተለያዩ ቦታዎች የመጣው ማኅበረሰብ ከሠራዊቱ ጋር ተቀናጅቶ ጁንታውን እግር በእግር እየተከታተለው ነው።
በቆንዲ አካባቢ ወደ ኩታ በር እየመጣ የነበረው የጁንታው ኃይልም በወገን ጦር ተመትቶ አብዛኛው ሙትና ቁስለኛ ሲሆን የሸሸውንም ለማስቀረት ሠራዊቱ ከሕዝቡ ጋር የተቀናጀ ትግል እያደረገ ነው።
ትናንት በጋሸና በኩል የመጣው ጠላትም በሠራዊታችን ክንድ ተደቁሶ የሞተው ሞቶ የተረፈው ለመሸሽ እየሞከረ ነው።
አሁን ጁንታው ያለ የሌለ ኃይሉ እየተመታበት በመሆኑ የመጨረሻውን የመጠባበቂያ ኃይል እየተጠቀመ ነው።
የማሠልጠኛ፣ የመሣሪያና እና የመገናኛ ማዕከላቱ በአየር በመመታታቸው የጁንታው ሠራዊት ከፊትና ከኋላ ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል።
በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ አካባቢዎች የዘመቱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይሉ፣ ከሚሊሻውና ከፋኖ ጋር በመሆን የጀመሩትን ተጋድሎ ማጠናከር ተገቢ ነው።
ሕዝቡም በሐሰተኛ መረጃዎች ከመወናበድ ይልቅ ድጋፉንና ትግሉን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀርቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.