በአይሰኢታና አርጎባ ህወሓት በንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 በአፋር ክልል በአወሲ ረሱ አይሰኢታ ከተማ ና አርጎባ ልዩ ወረዳ አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ የሚቃወም ሰልፍ ተካሂዷል።
በአርጎባ ልዩ ወረዳ ከተማ ጋቸኔ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራና በአፋር ንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረገ ያለውን ወረራና የንጹሃን ጭፍጨፋ እንዲሁም ሀገር የማፍረስ ሴራ በመቃወም ህዝቡ ድምጹን አሰምቷል።
በሰልፉቹ ላይ ህወሓት የኢትዮጵያ ጠላት ነው፣ ጁንታው በአማራና በአፋር ንጹሃን ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን፣ ለሀገራችን ሰላም ዘብ እንቆማለን እና ጁንታውን ለማጥፋት ከመንግስትና ከመከላከያ ጎን እንቆማለን የሚሉት መፈክሮች ተደምጠዋል።
ህዝብ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም በአስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ በማድረግ ስንቅ በማቅረብም ሆነ በመዝመት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተሳታፊዎች ጥሪ ማቅረባቸውን ከአርጎባ ልዩ ወረዳ የመንግስት ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!