የሀገር ውስጥ ዜና

የሰሜን ሸዋ ዞን የፖሊስና የሚኒሻ አባላት ወደ ወሎ ግምባር ዘመቱ

By Tibebu Kebede

October 23, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን የፖሊስና የሚኒሻ አባላት አሸባሪው ህወሀትን ለመደምሰስ ወደ ወሎ ግምባር ዘመቱ፡፡

ከዞኑ 27 ወረዳዎች የተውጣጡ የሚኒሻና የፖሊስ አባላት ዛሬ ሽኝት ተድርጎላቸዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላምና ደህንነት መምሪያ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ ለፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት የሽብር ቡድኑ ካልተወገደ ኢትዮጵያ ሰላም አታገኝም፤ ይህንን የሀገር ጠላት የሆነ ቡድን ለማስወገድ የጸጥታ አካላትን ወደ ግምባር ልከናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በወሎ ዘምተው ጅብዱ እየፈጸሙ ያሉ የሚኒሻና የፋኖ አባላት አሉ ያሉት አቶ ዋሲሁን ዛሬ የተሸኙት ሚኒሻዎችና የፖሊስ አባላት የአሸባሪውን አከርካሪ ሰብረው በድል እንደሚመለሱ እርግጠኛኞች ነን ብለዋል፡፡

ወደ ወሎ ግምባር የዘመቱ የጸጥታ አካላት እንደተናገሩት፥ ህዝባችንን ለሞትና ለመፈናቀል እንዲሁም ሀገራችንን ለማዋረድ የመጣውን የህወሀት የሽብር ቡድንን ደምስሰን የወንድሞቻችንን ሰላም እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!