Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ህግ ተላልፈዋል የተባሉ 53 የፀጥታ አካላት እንዲጠየቁ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ህግ ተላልፈዋል የተባሉ በ53 የፀጥታ አካላት እንዲጠየቁ መደረጉን የጎንደር ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ገለፀ።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲል ሰንደቁ ÷ በከተማዋ የእገታ ወንጀል፣ ህገ ወጥ የጥይት ተኩስና ተጀራጅቶ ዘረፉ ዋና ዋና የከተማዋ ወንጀሎች መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዚህ የእገታ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ 34 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ገልፀዋል።

አራት በእገታ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን አቶ ፉሲል ጠቁመዋል።

በከተማዋ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም የተባሉት 14 በየደረጃው በሚገኙ የፀጥታ አመራሮች 20 የፓሊስ አባላትና 14 የሚኒሻ አባላት ተጠያቂ መሆን መቻላቸውን ገልፀዋል።

የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ጥይት ተኩሰዋል የተባሉ 115 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልፀዋል።

ኃላፊው የተጀመሩ የሰላም የፀጥታ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ህብረተሰቡ ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ማለታቸውን ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.