የሀገር ውስጥ ዜና

ከድሬዳዋ 20 ኪ.ሜ ርቅት ላይ በመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ

By Tibebu Kebede

February 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከድሬዳዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ላስ ዴሬ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ በደረሰው የመኪና አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ በ5 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ7 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።