Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኩ ወደ ስራ የገቡ ባለሃብቶች ምርታቸውን ለገበያ እያቀረቡ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለአፍሪካ ሀገራት የተሰጠውን ከቀረጥና ኮታ ነፃ ዕድል ሳይጠብቁ ባላቸው የገበያ አማራጭ ምርቶቻቸውን ለአውሮፓ ሀገራት እያቀረቡ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኩ ሥራ አስኪጅ አቶ የሺጥላ ሙሉጌታ ገለጹ።
በፓርኩ ውስጥ ያሉ ስምንት የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ ለውጭ ባለሃብቶች መሸጋገራቸው ሥራ አስኪጁ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
ወደ ሥራ ከገቡት መካከል በስፔን ባለሃብት የተቋቋመው ኢኬ የጨርቃጨርቅ ማምረቻ ፋብሪካ አንዱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ የሺጥላ÷ በራሱ የገበያ ትስስር ምርቶቹን ለአውሮፓ ገበያ እያቀረበ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ፋብሪካው ባለፉት 3 ወራት ወደ ውጭ ከላካቸው የአልባሳት ምርቶች 2 ሚሊየን 475 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝቷል ነው የተባለው፡፡
ለአገር ውስጥ ተተኪ ምርቶችን እያቀረበ ያለው ፑርትማንት ብቅል ፋብሪካ ደግሞ በሩብ ዓመቱ 14 ሺህ ቶን ብቅል አምርቶ ለገበያ ማቅረቡን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.