የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 70ኛ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 70ኛ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የደቡብ ሱዳን የቅድመ መንግስት ምስረታ ሂደትን በዝርዝር ገምግሟል።
የሀገሪቱ ተቀናቃኝ ሀይሎች የክልሎችን ብዛት እና ወሰንን በተመለከተ እስካሁን መስማማት እንዳልቻሉ ተመልክቷል።
በተጨማሪም የሀገሪቱን ብሄራዊ ጦር ምስረታን በተመለከተም እንዲሁም ስምምነት ላይ አልደረሱም።
ምክር ቤቱ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የቀረው 13 ቀን መሆኑን በማንሳት እንደማይራዘም እና ሁሉም ተቀናቃኝ ሀይሎች በቀረው ጊዜ ልዩነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት እንዲደርሱ ነው ያሳሰበው።
በስብሰባው አሁን ላይ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በጋራ መከላከል የሚቻልበት ሁኔታንም ተመልክቷል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ ደግሞ 34ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
በስላባት ማናየ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision