የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዝደንት ፒተር ማውረር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፒተር ማውረር በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አመራሮች እንዲሁም ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሀላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳስታወቀው፥ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሳይወግንና በገልለተኝነት በመላ አገሪቱ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየጨመረ ስለመጣው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ምላሽ ላይ እንደሚወያዩ ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!