Fana: At a Speed of Life!

ጎህ የቤቶች ባንክ በይፋ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የባንኮች ታሪክ በሚሰጠው አገልግሎት የመጀመሪያ የሆነዉን ጎህ የቤቶች ባንክን በይፋ ስራ አስጀመሩ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ፥ዛሬ በአገራችን የባንኮች ታሪክ በሚሰጠው አገልግሎት የመጀመሪያ የሆነዉን ጎህ የቤቶች ባንክን” በይፋ ስራ አስጀምረናል ብለዋል።
በቤት ልማት ስራዉ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም አሁንም በፍላጎት እና አቅርቦት መካከል ያለዉ ከፍተኛ አለመጣጣም ተጨማሪ ስራዎች እንዲሰሩ አስገድዷልም ነው ያሉት።
በመሆኑም ዛሬ በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራውን ጎህ ባንክ ስራ ያስጀመርን ሲሆን፥ በቀጣይም መሰል የፋይናንስ ተቋማት ትኩረታቸውን የዜጎችን ህይወት በሚለዉጡ ተግባራት ላይ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል የምናደርግ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።
ወይዘሮ አዳነች አያይዘውም ባንኩ እንደ ከተማ በስፋት እየሄድንበት ላለው የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባርን ለመደገፍ ላበረከተው የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እያመሰገንኩ፥ በባንኩ ምስረታ ሂደት ዉስጥ ሀሳቡን ከማምጣት አንስቶ ዛሬ በይፋ ስራ እስኪጀምር የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያበረከታችሁ አካላት ልባዊ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
21
Engagements
Boost Post
19
1 Comment
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.