Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት ሰብዓዊ ድጋፎችን በማደናቀፍ ሕወሓትን ተጠያቂ ማድረግ አለበት – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሃንጋሪ፣ ጣልያን፣ ኔዘርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ሮማንያ፣ ስዊድን እና ስሎቫኪያ አምባሳደሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አቶ ደመቀ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሲያደርጉ ለቆዩት ሰብዓዊ ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

አንዳንድ የህብረቱ አባልሀገራት በመሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመቀበል ፈቃደኛ ባይሆኑም፥ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዋንና ዕውነታውን አስመልክታ ለአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን እና ለአባል ሃገራቱ ለማብራራት የምታደርገውን ጥረት በድጋሜ ገልፀዋል፡፡

መንግስት ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲል የተኩስ አቁም ስምምነትን እንደአማራጭ ቢያቀርብም፥ አሸባሪው የህወሓት ቡድን አለማክበሩን የአውሮፓ ህብረት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኢትዮጵያን አቋም ለመቀበል ፍቃደኛ አለመሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ማዕቀብ ለመጣል ያሳለፈው ውሳኔ ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብለዋል፡፡

በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ወረራ ፣ ግድያ እና ጥፋት ሲያደርስ የአውሮፓ ህብረት ዝምታን መምረጡ ኢትዮጵያን እንዳሳዘናትም አቶ ደመቀ ገልፀውላቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትግራይ ስታደርግ የቆየችውን ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ረገድ ቁርጠኝነት እንዳላት ገልጸው÷ የፍተሻ ኬላዎች ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር ማላላቱን እና ወደ ክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚደረጉ በረራዎች እንዲቀጥሉ ማድረጉን እንደአብነት አንስተው አስረድተዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት ለተረጂዎች የሚላኩ የሰብዓዊ ድጋፎችን በማደናቀፍ ሕወሓትን ተጠያቂ ማድረግ እንዳለበትም ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.