Fana: At a Speed of Life!

ከ18 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የመስኖ ግንባታና ማስፋፊያ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ከ18 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የአነስተኛ መስኖ ግንባታና ማስፋፊያ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
ግንቦት 2012 ዓ.ም በ7 ሚሊየን 1መቶ 46 ሺህ ብር የተጀመረዉ የጉሙ አነስተኛ መስኖ ግንባታ ሂደት 95 በመቶ መድረሱን የገለፁት የቤንሻንጉል ክልል ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የግንባታዎች ሥራ ሂደት አቶ አብዱ ሙሳ ÷ 34 ሄክታር መሬት የማልማት እና 78 አባ ወራዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም እንዳለዉ አስታዉቀዋል፡፡
በተመሳሳይ በአሶሳ ወረዳ የአምባ 11 ቀበሌ የመስኖ መስመር ማስፋፊያ ፕሮጀክት በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ በ11 ሚሊየን 2 መቶ 29 ሺህ ብር ዉል ተገብቶ ስራዉም 65 በመቶ መድረሱንም ገልፀዋል፡፡
በክልሉ ውሃ ስራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንትርፕራይዝ መሃንዲስ አቶ ሄኖክ ቸርነት በበኩላቸው ÷ በተቋሙ የሚሰሩ ግንባታዎች ጥራታቸውን ጠብቀው ለህብረተሰቡ የሚጠበቀዉን አገልግሎት እንዲሰጡ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በፕሮጀክቱም ከ80 በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም አስረድተዋል፡፡
የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎችም ከተቋሙ ጋር መስራት ከጀመሩ ወዲህ ኑሯቸዉን ከማሸነፍ ባሻገር ቤተሰቦቻቸውን መርዳት ችለዋል ሲል የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.