Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በመቶ ቀናት 108 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በ100 ቀናት ውስጥ በሚከናወኑ ስራዎች ዕቅድ ዙሪያ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡
በዚህም በ100 ቀናት ውስጥ 108 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን÷እቅዱን ለመሳካትም በአሰራር ስርዓት፣ በህግ ተገዥነት አመራር ልህቀት፣ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ልህቀት፣ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ አቅም ልማት እና ዘላቂ የገቢ እድገት ላይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ዝርዝር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በሌላ በኩል በአሰራር ስርዓት ላይ በሀገር ውስጥ ታክስ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚሰጡ ምላሾችን ወደ 85 በመቶ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች የሚሰጡ ምላሾችን ወደ 87 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱ ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ በሚገኙ አምስት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በኢ-ታክስ የሚያሳውቁ ግብር ከፋዮች ድርሻን ወደ 100 ፐርሰንት ለማድረስ እና የሀገር ውስጥ ታክስ ተገልጋይ ዕርካታን ወደ 78 በመቶ ለማሻሻል ዕቅድ መያዙ ተመላክቷል፡፡
1ሺህ 839 በስጋት የተመረጡ ማህደራትን የታክስ ኦዲት ለማከናወን፣ 114 በታክስ ማጭበርበር የተጠረጠሩ ማህደራትን የምርመራ ኦዲት ለማድረግ፣ የጉምሩክ ኢንተለጀንስ ውጤታማነትን ወደ 70 በመቶ ለማሻሻል አንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ መከላከልና መቆጣጠር ስራ ለማከናወን እቅድ መያዙንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.