Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የሀረሪ ክልል መንግስት የህዝብን ጥያቄን በመመለስ አደራውን መወጣት ይገባዋል – የክልሉ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የተመሰረተው አዲሱ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን የመረጠውን ህዝብ አደራ መወጣት ይገባል ሲሉ የሀረሪ ክልል ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት በተለይ ለህዝብ አንድነት እንዲጠናከር፣ ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራና የነዋሪውን የኑሮ ውድነት መቀነስ ላይ ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡ መካከልም አቶ ደበሮ ቴንኬሎ ፥ህዝቡ አዲሱ መንግስትን ሲመርጠው ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲያገኝ በመሆኑ አዲሱ አመራር የህዝብን ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ከማድረግ አንፃር ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን የህዝብን አደራ በአግባቡ መወጣት ይገባል።
በተለይም ህዝብን እያማረረ የሚገኘው የኑሮ ውድነት እንዲቀንስ ልዩ ትኩረት መስጠት እንዲሁም ከስራ እድል ፈጠራ ጋር ተያይዞ አዲሱ የክልሉ መንግስት እስከታችኛው እርከን በመውረድ የሚሰሩ ስራዎችን መፈተሽና መገምገም አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ጃሚዕ ሄደር በበኩላቸው፥ አዲሱ የተመረጡ የክልሉ አመራሮች እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና ለአንድ አላማ በመቆም ክልሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ ይገባል።
ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን በማረም እና ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም በክልሉ በገጠርና በከተማ የሚገኘውን ህዝብ ተጠቃሚየሚ ያደርጉ ተግባራትን በማከናወን ህዝብ የሰጠውን አደራ መወጣት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል።
ህዝቡም በሚከናወኑ ተግባራት ድጋፉን በማጠናከር አዲሱ መንግስት ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ሀረሪ ክልል የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ ከመሆኗ አንፃር ሁሉንም ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን ማከናወን አዲስ ከተመሰረተው የክልሉ መንግስት እንደሚጠብቁ የተናገሩት ደግሞ አቶ ተክሉ መታፈሪያ ናቸው።
እየጎለበተ የሚገኘው የክልሉ ሰላም የበለጠ እንዲጠናከር፣ ከኑሮ ውድነት እንዲቀንስና ሌብነትን ከመከላከል አንፃር ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል፤ ለዚህም ህዝቡ ተሳትፎውን ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
ሌላው አስተያየት ሰጪ ወጣት ሙላው ገብረህይወት፥ አዲሱ መንግስት በተለይም የክልሉን ሰላምን በማጠናከር የወጣቶች ስራ አጥነት ችግር ትርጉም ባለው መልኩ ይቀርፋል የሚል እምነት እንዳለው ተናግሯል።
በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቀነስ ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ ነው ያለው ወጣት ሙላው፥ ከኑሮ ውድነት ከመቅረፍ አንፃርም የኑሮ ውድነት እንዲባባስ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥርና ክትትል ማጠናከር ይገባል ማለቱን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.