የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሰራዊት አባላት ለተማሪዎች ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነቀምት ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚኖሩ ተማሪዎች የምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የሰራዊት አባላት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡
የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮሎኔል ቢረሳው ሽፈራው ÷ ሰራዊቱ ግዳጁን በሚወጣበት አካባቢ ሁሉ ህዝባዊነቱን በተግባር የሚገለፅበትን ስራ እንደሚያከናውን ገልፀው ይህም አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።
የነቀምት ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ሀላፊ ወይዘሮ መስከረም አለማየሁ በበኩላቸው ÷የትኛውም የስራ ዓይነት መስዕዋትነትን የሚጠይቅ ቢሆንም ሰራዊትነት ከተረፈው ሳይሆን ካለው ላይ የሚያካፍል ነው ብለዋል።
ስለተደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችና ወላጆችም ÷ በሰራዊቱ የተደረገላቸው ድጋፍ በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!