የዜጎች ሕይወት እንዲሻሻል እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩና ገቢያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ቁጠባ ወሳኝ የሕይወት መርህ እንዲሆን እንሰራለን ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናገሩ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ያዘጋጀውና ለ45 ቀናት የሚቆየው “ለተሻለ ነገ ዛሬ ይቆጥቡ” የተሰኘው አገር አቀፍ የቁጠባ ንቅናቄ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
የምርት ምጣኔና ቁጠባ ለአገራዊ እድገት ያላቸው አስተዋጽኦ ሚዛኑን እንዲጠብቅ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ተናግረዋል፡፡
የተረጋጋ ሕይወት መምራትና ሃብት ማፍራት እንዲቻል የቁጠባን ባህል ማዳበር እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።
ለዚህም ተከታታይና ሰፊ የሕዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር 3ኛው አገር አቀፍ የቁጠባ መርሃ ግብር መጀመሩን ገልጸዋል።
እ.አ.አ 2018 የኢትዮጵያ አገራዊ ቁጠባ ወይም ወደ ባንኮች የገባ የቁጠባ ገንዘብ 638 ቢሊየን ብር ሲሆን በ2021 ወደ 1 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር ማደጉንም አቶ አቤ ሳኖ ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!