Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኖርዌይ እና ካናዳ ጠቅላይ ሚኒስሮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ   እና ካናዳጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ  ጋር ተወያዩ
 
በውይይቱ ላይም የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል ፣ የሴቶች ፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋዬ እና የሲ ኤን ኤን የ2019 ጀግና ፍሬወይኒ መብርህቱ እንዲሁም ሌሎች ሴት አመራሮች ተገኝተዋል።
 

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚነስትር ጋር በነበራቸው ቆይታ ሴቶች በኢኮኖሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል በፓለቲካው እና ስራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም በሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ዙሪያ በማተኮር ውይይት አድርገዋል።

በሴቶች ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲሁም ሴቶችን ለማብቃት የሚከናወኑ ተግባራትን የካናዳ መንግስት እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

የሴቶችን ሚና ከማሳዳግ እና ወጣቶችን ከማብቃት አኳያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ እና በጋራ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ተወያይተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም በማተኮር መወያየታቸው  ተገልጿል፡፡

ከዚህ በኋላም ሁለቱ ሀገራት በጥምረት ለመስራት የሚያስችሏቸውን አሰራሮች እንደሚዘረጉም ተነስቷል፡፡

ኢትዮጵያና ካናዳ ለረጅም ጊዜያት በበርካታ ዘርፎች በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውም ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ እንደምትገኝ መታዘባቸውን  ገልጸዋል፡፡

በተለይ ደግሞ ለሴቶች የተሰጠውን የአመራር ዕድል  ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድንቀዋል፡፡

ከዓለም ነበራዊ ሁኔታ በመነሳት ሀገራቱ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰሩ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ቱሩዶ ተናግረዋል፡፡

 

በዘቢብ ተክላይ

 

 

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.