የሀገር ውስጥ ዜና

የደሴ ከተማ ወጣቶች አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ወደ ግንባር ተንቀሳቀሱ

By Meseret Awoke

October 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ ወጣቶች አሸባሪውን ህወሓት ለመደምሰስ ወደ ግንባር እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

አሸባሪው ቡድን ለዓመታት አብዝቶ በደል ሲያደርስባቸው የቆዩት የደሴ ከተማ ወጣቶች “በድጋሚ የበደልን ቀንበር ልንሸከምበት የምንችልበት ምክንያት የለም” ብለዋል፡፡

በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የሰለጠኑ እና የተደራጁ ወጣቶች ህወሓትን ለመደምሰስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡

የከተማዋ ወጣቶች የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ዘራፊ ቡድን ወሎ ላይ እንቀብረዋለን ሲሉ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

የደሴ ከተማ ወጣቶች ተወካይ አስተባባሪ እንደገለፁት÷ ኢትዮጵያን የማዳን ተግባሩን ስኬታማ ለማድረግ ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡

በዘሩ ከፈለኝ እና አዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!