አራተኛው የቻይና የንግድ ትርኢት ለኢትዮጵያ ቡና ግብይት ሰፊ እድል ይዞ መጥቷል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አራተኛው ዙር የቻይና የውጭ ንግድ ትርኢት ለኢትዮጵያ የቡና ግብይት ሰፊ እድል ይዞ መምጣቱ ተነገረ።
በኢትዮጵያ ትልቁ የቡና አምራችና ላኪ ቅርንጫንፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ እስራኤል ደገፋ ከሺንዋ ጋር በነበራቸው ቆይታ ድርጅታቸው በትርኢቱ በመሳተፍ የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም እና ጥራት ያለው ቡና እንደሚያስተዋውቅ ገልጸዋል።
በቻይናዋ ሻንጋይ ግዛት የሚካሄደው የቻይና የውጭ ንግድ ትርኢት እያደገ የመጣውን የኢትዮ ቻይና የቡና ግብይት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” ብለዋል።
“ከፍተኛ ግብይት ከሚፈጽሙ አካላት ጋር ለመገናኘትና ለቻይናውያን የዘርፉ ባለሃብቶች የኢትዮጵያ ቡና ከሌሎቸ ጋር ያለውን ልዩነት ለማስተዋወቅ የንግድ ትርኢቱ የላቀ ሚና ይጫወታል” ሲሉ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያን ቡና ከሚገበዩ አስር ከፍተኛ ገዢዎች ውስጥ ቻይና እንደምትገኝበት መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!