በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዎዳ የብረት ኢንዱስትሪን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እንዲሁም የሚመለካታቸው አካላት ዎዳ የብረት ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝቱም በኋላ ሃላፊዎቹ ከፋብሪካው አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን÷ በምርት ሂደት ስለገጠሙ ችግሮች እንዲሁም በማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ዎዳ የብረት አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሰበታ ከተማ የሚገኝ እና በሶስት ፌዝ 65 ሚሊየን ዶላር ፈሰስ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለ አምራች ድርጅት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ድርጅቱ ከውጭ አገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገቡትን የብረት ነክ ምርቶች ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት አስቦ እየሰራ መሆኑን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!