Fana: At a Speed of Life!

የናይጀሪያ ኮሌጅ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጀሪያ ጉምሩክ ሰራተኞች ማሰልጠኛ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የጉምሩክ ኮሚሽን የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው።
የልዑካን ቡድኑን የኮሚሽኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ፥ የጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ “የእንኳን ደህና መጣችሁ“ መልእክት አስተላልፈዋል።
ምክትል ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ እና የናይጀሪያ ይፋዊ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ረጅም ዘመን ያስቆጠረ መሆኑን አስታውሰው፥ ሁለንተናዊ ትስስሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጉምሩክ ኮሚሽን ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል ብለዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ያከናወናቸውን ተጨባጭ ለውጦች እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተሰሩ ስራዎችን በሚመለከት በኮሚሽኑ የለውጥ አማካሪ በአቶ መንግስቱ ተፈራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በሚኖራቸው የአምስት ቀናት የስራ ጉብኝት የተመረጡ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን የስራ እንቅስቃሴ እና ከኮሚሽኑ ጋር ግንኙነት ያላቸውን መንግስታዊ ተቋማት እና የሙያ ማህበራትን እንደሚጎበኙ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+5
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.