የሀገር ውስጥ ዜና

የደባርቅና አካባቢው ተወላጆች “አብሮ አደግ” ማኅበር ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

October 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ የደባርቅና አካባቢው ተወላጆች “አብሮ አደግ” ማኅበር በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

ማኅበሩ በአዲስ አበባ ከሚኖሩ የደባርቅና አካባቢው ተወላጅ አባላቱ በሰበሰበው 104 ሺህ ብር በላይ ወጪ 29 ኩንታል ፊኖ ዱቄት በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የደባርቅና አካባቢው ተወላጆች ድጋፉን በአብሮ አደግ ጓደኛቸው አቶ ዮሐንስ ባዬ በኩል ለሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስረክበዋል፡፡

ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው 186 ተፈናቃይ ወገኖች መድረሱ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በዞኑ የሚፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የገለጸው የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ÷ በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ የሰሜን ጎንደር ዞን ተወላጆች ለወገናቸው ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!