የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

October 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስታር ማክፋይል ጋር በተለያዩ አገራዊ የልማት ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው በተለይም በአሁኑ ወቅት መንግስት በከተሞች የሚታየውን የሥራ አጥነት፣ የመኖሪያ ቤት ዕጥረትና ከሰላም ጋር በተያያዘ እያደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጥረት በተመለከተ መክረዋል፡፡