የሀገር ውስጥ ዜና

በከተሞች ፅዳትና ውበት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ተባለ

By Feven Bishaw

October 26, 2021

አዲስ አበበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት የቤቶችና የከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሄኖስ ወርቁ÷ ከተሞች በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አረንጓዴ ልማት ስራ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ቆሻሻ ሃብት ነው ያሉት አቶ ሄኖስ÷ሚኒስቴሩ ከከተሞች ቆሻሻ ኮምፖስት እንዲመረት በማድረግ ለአረንጓዴ ልማት እንዲውል እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።