የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሓት በደቡብ ወሎ ዞን ሰርጎ በገባባቸው ስፍራዎች አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ ነው

By Feven Bishaw

October 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በደቡብ ወሎ ዞን ሰርጎ በገባባቸው ስፍራዎች ላይ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ÷ በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ፣ በፌዴራል ፖሊስ ፣ በአማራ ልዩ ሀይል ፣ በፋኖ እና በሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጥምረት አሸባሪው የህወሓት ቡድን አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መሆኑን ተናግረዋል::