Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ተመድ በሀገሪቱ እያከናወናቸው ላሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች – አቶ ደመቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀንን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በተካሄደው ስነ ስርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ በመንግስታቱን ድርጅት ቻርተር ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ማጉላት እና ድርጅቱ በኢትዮጵያ እያከናወናቸው ላሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ኢትዮጵያ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አቶ ደመቀ ተናግረዋል፡፡

መንግስት በኢትዮጵያ እና በተመድ መካከል በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግባባት ለመፍጠር እያደረገ ያለውን ጥረትም አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች አባል እንደመሆኗ÷ አላማዋን ከግብ ለማድረስ የበኩሏን በመወጣት እንደምትቀጥልም ገልጸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተመድ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የአፍሪካ ሕብረት ተወካዮች መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የተባበሩት መንግስታት ቀን ጥቅምት 24 ቀን 1945 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በይፋ መጀመሩን ተከትሎ ታስቦ የሚውል ቀን ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.