Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ሙቀት መጠን በ2 ነጥብ 7 ዲግሪ ሴልሼስ መጨመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የሙቀት መጠን በ2 ነጥብ 7 ዲገሪ ሴልሽየስ መጨመሩን የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት አመላክቷል፡፡
 
በተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም የከባቢ አየር ሙቀት መጨመርን አስመልክቶ በስኮትላንድ ዋና ከተማ ግላስጎ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ አሁን ላይ የዓለም የሙቀት መጠን በአሳሳቢ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ድርጅቱ ባቀረበው ሪፖርትም በከባቢ አየር የሚለቀቅ በካይ ጋዝን ለመቀነስ የተቀመጡ እቅዶች ደካማ መሆን ለአለም የሙቀት መጨመር ምክንያት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡
 
በተለይም የበካይ ጋዝ ልቀት መጠንን ለመቀነስ የተደረጉ ዓለማቀፋዊ ሰምምነቶች ተግባራዊ አለመደረጋቸው ችግሩን ይበልጥ አባብሶታል ነው ያለው፡፡
 
ይህን ተከትሎም አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት የሙቀት መጠን በአማካይ በ2 ነጥብ 7 ዲግሪ ሴልሼስ መጨመሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
 
በመድረኩ የቡድን 20 አባል ሀገራት 78 በመቶ የሚሆነውን በካይ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር በመልቀቅ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚወስዱ ድርጅቱ ይፋ አድርጓል፡፡
 
አባል ሀገራቱ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል የተገቡትን አባዛኛውን የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃ አለመተግበራቸው የተገለጸ ሲሆን ÷ በቀጣይም ህጎችን ተፈፃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡
 
የአለም ሙቀት መጠንን ከ2 ነጥብ 7 ዲግሪ ሴልሼስ ወደ1 ነጥብ 5 ለመቀነስ በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደዉ ኮንፈረንስ ላይ ተመድ የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
 
 
ምንጭ÷ አልጀዚራ
 
 
በሚኪያስ አየለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.