ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነቷን እንድትቀጥል የአሜሪካ ኤምባሲ እገዛ እንዲያደርግ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሺነር ለሊሴ ነሜ ከአሜሪካ ኤምባሲ ከፍተኛ የንግድ ባለሙያ ያሱኢ ፓይ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነቷን እንድትቀጥል የአሜሪካ ኤምባሲ ከኮሚሽኑጋር በቅንጅት በመስራት እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
አጎዋ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ሴክተር ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥቅም እና በኢንቨስትመን ሴክተሮች ለተሰማሩ አካላት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ መገለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!