Fana: At a Speed of Life!

ዶሮና የዶሮ ውጤት ዋጋ መናር ምርቱን የቅንጦት ምግብ እንዲሆን አድርጎታል-ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የዶሮ ሃብት ልማትና እና ግብይት ረቂቅ አዋጅ ማዳበር የሚያስችል ግብዓት መሰብሰቢያ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱም ዶሮና የዶሮ ውጤት ዋጋ መናር ለኢትዮጵያውያን የቅንጦት ምግብ እንዲሆን አድርጎታል ሲሉ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ ገልጸዋል፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት ያስችል ዘንድ የዶሮ አረባብን ለማዘመን የሚያግዝ አሰራር መከተል አስፈላጊ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ለዚህም የዶሮ ሀብት ልማትን በህጋዊ ስርዓት በመምራት ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም ከፍ ለማድረግ የወጡ አዋጆችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በውይት መድረኩ ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት ዶ/ር ፍቅረማርቆስ መርሱ በበኩላቸው÷ የዶሮ ሃብት ልማት የዳሰሳ ጥናትና የግብይት ስርዓት ሰንሰለቱን በተመለከተ በተደረገ ጥናት ውጤት መነሻ የተዘጋጀ መሆኑን ዶክተር ፍቅረማርቆስ መርሱ ገልጸዋል፡፡

በአዋጅ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ተሳታፊዎችም የግብይት ስርዓቱ ህገወጥ አሰራሮችን የሚቆጣጠርና ህብረተሰቡም በተመጣጣኝ ዋጋ ዶሮንና የዶሮ ውጤት በማግኘት ተጠቃሚ የሚያደርግበትን አሰራር የሚፈጥር መሆን እንዳለበት መጠቆማቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.