በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
አደጋው በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በገርቢ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀልቀልቲ በሚባል ቦታ ትናንት ከለሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ መከሰቱን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ተናግረዋል፡፡
የትራፊክ አደጋው የተከሰተውም ታርጋ ቁጥሩ A-21594 የሆነ የጭነት አይሱዙ መኪና ከሸዋሮቢት ወደ ኮንቦልቻ ቲማቲም ጭኖ ሲሄድ በነበረበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ሹፌሩን ጨምሮ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን ነው የተናገሩት ሃላፊው÷በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡
ማንኛውም አሽከርካሪ በጥንቃቄ በማሽከርከር ከሚደርሰው የትራፊክ አደጋ እራሱንና ንብረቱን ሊከላከል እንደሚገባ ጥሪ መቅረቡን ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!