Fana: At a Speed of Life!

18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የኢኖቬሽን አፍሪካ ዲጂታል ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በጉባኤው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላን ጨምሮ ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የቴክኖሎጂ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የኤምባሲ ተወካዮች እና ተጋባዥ እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
 
ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችሉ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን ተናግረዋል።
የቴሌኮም ዘርፍን በከፊል ወደ ግል ማዞር፣ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችንና የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከላትን መደገፍ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የዲጂታል ክፍያ፣
የዲጂታል እውቀት ላይ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።
የጸደቀው የኢ-ትራንዛክሽን አዋጅ፣ በረቂቅ ላይ ያሉት የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ፣ የስታርት አፕ አዋጅ፣ የኢኖቬሽን ፈንድ አዋጅ፣ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ በዘርፉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ትልቅ አቅም ይፈጥራሉ ተብሎ እንደታመነባቸው ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
 
በአይሲቲና ቴሌኮም ዘርፍ ላይ የሚያማክረው ኤክስቴንሽያ ሊሚትድ ዋና ስራ አስኪያጅ ታሪቅ ማሊክ÷ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የአፍሪካ ሀገራት የአይሲቲ ዘርፍ ማሻሻያ ላይ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል።
 
በጉባኤው የህግ ማዕቀፎች፣ መሰረተ ልማት፣ ፈጠራ የታከለባቸው የንግድ ስራዎችና አካታችነች ላይ እንደሚመክሩ መናገራቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ይህ ጉባኤ አፍሪካን ዲጂታል ለማድረግ፣ በተለያዩ ዘርፎች ተመራጭ እንድትሆን የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.