በአማራ ክልል በኩታ ገጠም የለማ የሩዝ ማሳ ተጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ዘንዘልማ ቀበሌ በ519 አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የለማ የተሻሻለ የሩዝ ምርት ማሳ ተጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ እንደተገለጸው÷ በዘንዘልማ ቀበሌ 217 ሄክታር መሬት በሩዝ ምርት የለማ ሲሆን÷ ከዚህም 10 ሺህ ኩንታል የሩዝ ምርት ይጠበቃል፡፡
በአማራ ክልል 55 ሺህ ሄክታር መሬት በሩዝ ምርት መሸፈኑን÷ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃልኪዳን ሺፈራዉ ገልጸዋል፡፡
አርሶአደሩ ካመረተ በኋላ የገበያ ችግር እንዳይገጥመውም÷ ከፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ስልጠና ማእከል ጋር በመተባበር እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በፎገራ ብሄራዊ የሩዝ ምርምርና ስልጠና ማእከል የቀረበ ‹‹ሻጋ›› የተሰኘ የተሻሻለ የሩዝ ዝርያ በሄክታር ከ44 እስከ 56 ኩንታል ምርት ይሰጣል ተብሏል ሲል ኢ ፕ ድ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!