Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ በታማኝነት ማገልገል እና ሃላፊነቱን መወጣት አለበት- አቶ ሽመልስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሩ ህዝብ የሰጠውን አደራ ጠብቆ በታማኝነት ማገልገልና ሃላፊነቱን በሚገባ መወጣት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ።
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሶስት ወራት የተከናወነው የመንግስት ስራ አፈጻጸም በአዳማ ከተማ እየተገመገመ ነው።
በመርሃ ግብሩ ካለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ወዲህ በተከሰተው ለውጥና ተግዳሮቶች እንዲሁም የአንደኛ ሩብ ዓመት የመንግስት ስራ አፈጻጸምና በቀጣይ በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል፡፡
ሀሉም አመራር የተሰጠውን ሃላፊነት በታማኝነትና በብቃት ለህዝብ መስራት እንደሚጠበቅበትም ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ ከአዲስ መንግስት ምስረታ በኋላ በክልል፣ በዞንና በከተሞች የተሾሙ አዳዲስ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።
በዛሬው ዕለት ለውይይት በቀረቡ መነሻ ጽሁፎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷ በዚህም በተጨባጭ ወቅታዊ ክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡
 
በረጋሳ ፍሮምሳ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.