የባቡር ሃዲድ ብረት የሰረቁ ግለሰቦች ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ የባቡር ሃዲድ ብረት የሰረቁ ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የአዳማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ እንደገለፁት÷ ስርቆቱ የተፈፀመው በአዳማ ከተማ ልዩ ስሙ ኬላ በሚባል አካባቢ ነው።
ነሐሴ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ተከሳሽ ሬድዋን አህመድና ዘርዬ ጥሩነህ የሚባሉ ግለሰቦች አሮጌውን የባቡር ሃዲድ ብሎን በመፍታት 250 የባቡር ሃዲድ ዘንግ መዝረፋቸው መረጋገጡን ገልጸዋል።
የዘረፉትን ንብረት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-01471 አ.አ በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጭነው ለመሰወር ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፖሊስና ዐቃቤ ሕግ ተጣርቶ የቀረበለትን ማስረጃ ግራ ቀኙን በመመልከት ዛሬ በዋለው ችሎት ግለሰቦቹ እያንዳንዳቸው በአራት ዓመት ፅኑ እስራትና በ8 ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!