Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ ለህልውና ዘመቻው ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ለህልውና ዘመቻው ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
 
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አካሉ ወንድሙ እንደገለጹት ÷ ለህልውና ዘመቻ ድጋፍ ከህብረተሰቡ 57 ሚሊየን 82 ሺህ 817 ብር ተሰብስቧል ፡፡
 
ከንግዱ ማህበረሰብ 19 ሚሊየን ብር በላይ፣ ከከተማ ነዋሪው 4ሚሊየን ብር፣ እንዲሁም ከአርሶ አደሮች 364 ሺህ 380 ብር መሰብሰቡን ነው የገለጹት፡፡
 
በተጨማሪም ከመንግስት ሰራተኞች 32 ሚሊየን 849ሺህ ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
 
የከተማዋ ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው የሚያደረጉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ከንቲባው ጥሪ ማቅረባቸዉን ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.