ወገን ጦር በወሰደው እርምጃ አሸባሪው ቡድን እየተሽመደመደ መሆኑን ተመልክቻለሁ-የአብን ም/ሊቀመንበር
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴና አካባቢው ወጣቶች ለወገን ጦር ውጤታማ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር የሱፍ ኢብራሂም ገለጹ፡፡
ጦርነቱ በሚካሄድበት ቦታ የሚገኙት አቶ የሱፍ ኢብራሂም ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት፥ የወገን ጦር በጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ አሸባሪው ቡድን መራመድ በማይችልበት ደረጃ እየተሸመደመደ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል፡፡
መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻው ገዢ ቦታዎችን በመያዝ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊ ኪሳራ እያደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ የሱፍ እንዳሉት የደሴ ከተማ፣ የኩታበር፣ የተሁለደሬ እና አካባቢው ወጣት ምሽግ ድረስ በመግባት ውኃ፣ ትጥቅ እና ስንቅ እያቀረበ ነው፡፡
ከዚያ ባለፈም ለወገን ጦር መረጃ በመስጠት ድጋፉን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው ያሉት፡፡ በዘመቻውም የማኅበረሰቡ እገዛ ከፍተኛ እንደሆነ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
የወገን ጦርን ሕዝቡ በሚገባው ልክ በመደገፉ ጠላት ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ እንዲቀር ማድረጉንም አስረድተዋል፡፡
ጦርነቱ ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ ከተነሳ ባንዳ ጋር በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለትግሉ በመረባረብ የሚጠበቅበትን ኀላፊነት መወጣት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የችግሩን ግዝፈት በሚገባ በመገንዘብ በስንቅና ትጥቅ አቅርቦት፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋም ሂደቱ መላው ኢትዮጵያውያን በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው አቶ የሱፍ ጠይቀዋል፡፡
ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወረራ የፈጸመውን የጠላት ኀይል ለመመከት አሁንም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ግንባር መክተት አለባቸው ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!